የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የውሃ ታሪፍ ማሻሻያ

መግቢያ
የሀረር ከተማ የመጠጥ ውሀ ሶስት መገኛዎች ያሉት ሲሆን እነሱም በ72 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ሀሰሊሶ እና ሁላሁሉል ፤ በ23 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ሀረማያ ኢፋ ባቴ እና በ20 ኪ.ሜ ርቀት የሚገኘው የኤረር መጠጥ ውሃ ናቸው፡፡
የሀሰሊሶ እና ሁላሁሉል የውሃ ምንጮች ከፊል የድሬዳዋ ገጠር ቀበሌዎችንና ደንገጎን፤ አዴሌ፤ለሀረማያ እና አወዳይ ከተሞች እንዲሁም ለሐረር ከተማ ነዋሪዎች ውሃ እየሰጠ ያለ ነው፡፡ በኢፋ ባቴ የሚገኘው የውሃ ምንጭ ለሐረር ከተማ ህዝብ በቦቴ ውሀ አቅርቦት የሚያገለግል ውስን ውሀ ነው፡፡ የኤረር መጠጥ ውሃ በሐረሪ ክልል የሚገኙ ገጠር ቀበሌ አካባቢዎች በከፊል ውሃ እየሰጠ የሐረር ከተማን የንፁህ የመጠጥ ውሀ በከፊል ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው፡፡
በከተማው የሚስተዋሉ መስፋፋት እንዲሁም እያደገ የመጣውን የህዝብ ቁጥር የውሃ ፍላጎት ጥያቄዎችን ሊመልስ የሚችል የውሃ አቅርቦት ጥናት የሚያስፈልገው ቢሆንም ያለውን የውሃ አቅርቦት አስተማማኝና ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የሀረር ከተማ የውሃ አቅርቦት ዘላቂ መፍትሄ እስከሚያገኝ አስተዳደራዊ ወጪ፣ የኦፕሬሽንና የጥገና ወጪ በራሱ
የውሃ ሽያጭ መሸፈን ባለመቻሉ ምክንያት በ2012 ዓ.ም ፀድቆ በ2014 ዓ.ም የካቲት ወር ላይ ተግባራዊ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ወቅታዊ የታሪፍ ጥናት ባለመሆኑ አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋርም አብሮ የማይሄድ ነው፡፡ በመ/ቤቱ ገቢ ላይም ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት አልቻለም፡፡ ስለዚህ አሁን ካለው የገበያ ሁኔታ ጋር አብሮ መሄድ የሚችል እንዲሁም የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ክለሳ ማድረግ አሰፈልጓል፡፡
የባለሥልጣን መ/ቤቱ የታሪፍ ለውጥና ማሻሻያ የተደረገበት ዝርዝር ምክንያቶች፡-
አሁን በስራ ላይ ያለው ታሪፍ ከተጠና ቆይቶ የተተገበረ በመሆኑ፤
አስተዳደራዊ ፣ የኦፕሬሽን እና የጥገና ሥራ ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ በመምጣቱ፤
የውሃው ሲስተም በዓይነቱ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሚያደርገው ውሃውን ከድሬዳዋ ሀሰሊሶና ሁላ ሁሉል ወደ ደንገጎ ከ1000 ሜትር ከፍታ በላይ ለመግፋት የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ ኃይል ግዙፍ በመሆኑ ይህም ከ6 – 8 ሜጋ ዋት ማስፈለጉ፤
ጠቃሚ መረጃዎች
የውሃ ፍጆታ ክፍያ ወር በገባ ከ1 እስከ 25
የክፍያ ቦታዎች:-
- በዋናው መ/ቤት
- ፤በጀጎል በ06 ቀበሌ የድሮው ቴሌ አካባቢ ፤
- ጁንየር ት/ቤት በታችኛው በር (እስቴድየም አካባቢ)
እና በተለያዩ ባንኮች:-
- በCBE Birr፤
- በአበሲኒያ ባንክ፤
- በአንበሳ ባንክ ፤
- በቴሌ ብር እና
- በአዋሽ ባንክ መክፈል ትችላላችሁ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፣ አስተያየትና ጥቆማዎችን በ8180 ነፃ የስልክ ጥሪ ይደውሉ፡፡
ተቋሙ በክልል ደረጃ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመንና ከሌሎች አቻ የውሃ ተቋማት ጋር ራሱን ችሎ ተወዳዳሪ እንዲሆን የሚያስችል የመዋቅር ማሻሻያ ማስፈለጉ፤
በባለሥልጣን መ/ቤቱ የሚያስተዳድረው ሲስተም የቧንቧ መስመሮች ረጅምና ትላልቅ ስፋት ያላቸው በመሆኑ መደበኛ የኦፕሬሽንና ጥገና ማከናወኛ መሳሪያዎች መለዋወጫ ከፍተኛ ወጪ ማስፈልጉ፤
የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሲስተሙ መለዋወጫዎቹ በሀገር ውስጥ በቀላሉ የማይገኙ ለጥገናም ከፍተኛ ወጪና ከፍተኛ የሠለጠነ የሰው ኃይል ስለሚያስፈልግ ይህም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ በመሆኑ፤ ከላይ በተመለከተው መልኩ የታሪፍ ማሻሻያው በጥናት ሊሻሻል ችሏል፡፡
ውሃ በቁጠባ እንጠቀም!
ማሳሰቢያ፡-
በህገ ወጥ መንገድ ከውሃ ቆጣሪ በፊት ውሃን መጠቀም እና መቆጣጠሪያ ቁልፍ (Gate Valve) መቀየር የገንዘብ ቅጣት እስከ ከደንበኝነት መሰረዝ እንዲሁም በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፡፡
