የሐረር ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የተሰጠ መግለጫ

በክልሉ የንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ በ350 ሚሊየን ብር የተለያዩ ፕሮጀክቶች እያከናወነ መሆኑን የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ። በሀረሪ ክልል የንፁህ የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ በ350 ሚሊየን ብር የተለያዩ ፕሮጀክቶች እያከናወነ መሆኑን የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የክልሉ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ዲኒ ረመዳን ባለስልጣኑ በ2016 የበጀት አመት ከመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ለማከናወን በታቀዱ ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ መግለጫ ተሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በተያያዘ 2016 የበጀት ዓመት በክልሉ በከተማም ሆነ በገጠር የንፁህ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን ለማሳደግ እና አቅርቦትን ለማሻሻል በ350 ሚሊየን ብር ወጪ የተለያዩ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል፡፡ የውሀ ምርትን ለማሳደግ ከድሬደዋ እና ከኤረር አካባቢ የሚመጣውን የውሃ ምርት ማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርፀው እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በክልሉ ካለው ፍላጎት አንፃር እየቀረበ የሚገኘው የንፁህ መጠጥ ውሃ ምርት ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ በአሁኑ ወቅት በፈረቃ በ15 ቀን እየቀረበ የሚገኘው የንፁህ መጠጥ ውሃ ምርት ወደ 7 ቀን ለማውረድ መታቀዱን አስረድተዋል፡፡ ለዚህም ተጨማሪ ጉድጓዶችን በመቆፈር በአሁኑ ወቅት ከሚመረተው የውሃ መጠን በእጥፍ ለማሳደግ ውጥን ተይዟል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም በሳኒቴሽን ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት ከ100 ሚሊዩን በሆነ ወጪ በ6 ወረዳዎች ላይ 90 የሚሆኑ የህዝብ እና የማህረሰብ መፀዳጃ ቤቶችን ለመገንባት፤ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚወጡ ፍሳሾችን በአግባቡ እንዲወገድ ለማድረግ እንዲሁም የውሀ ብክለትን ከመከላከል አኳያ በበጀት አመቱ በትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከመልካም አስተዳደር እና ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮችን ለመቅረፍም ሁለት ተጨማሪ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን በአራተኛ እና በጃጎል 06 ቀበሌ በመክፈት አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ስለመቻሉ ጠቅሰዋል።
በዘላቂነት የከተማዋን የመጠጥ ውሀ ችግርን ለመቅረፍ የክልሉ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶችን እየተደረጉ መሆኑንም ገልፀዋል
