
ብልፅግና ፓርቲ የዜጎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማቃለል በተከናወነው ስራ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ይገኛል ሲሉ አቶ ጌቱ ወዬሳ ተናገሩ።
የሀረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያስገነባው የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ለተጠቃሚዎች አስረክቧል።
የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ፓርቲያችን ብልፅግና ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በበጎ ፈቃድ ተግባር ሰው ተኮር የሆኑ ማህበሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በዚህም በክልሉ የዜጎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለማቃለል በከናወነው ስራ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በጎ ፈቃድ በሌሎች ደስታ መደሰት መሆኑን የገለፁት አቶ ጌቱ ማህበረሰቡን እና አካባቢን መሰረት ባደረጉ የአካባቢ ጥበቃ እና የዜጎችን ኑሮ ለማቅለል የተጀመሩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን በበኩላቸው በበጀት አመቱ ተቋሙ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል ።
በተለይም በክረምት በጎ ፍቃድ ስራ ለበርካታ አቅመ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ፣ ማእድ ማጋራት እንዲሁም ለአቅመ ደካማ ማህበረሰብ የቤት እድሳት እና ግንባታ ማድረገቸውን ተናግረዋል።
በዛሬው እለትም በድሬ ጠያራ ወረዳ ሱቁል ቀበሌ ያስገነባው ሁለት ቤቶች ለተጠቃሚው ማስተላለፋቸውን ነው የተናገሩት
በቀጣይም ተቋሙ የዜጎችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የማቃለሉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
