Blog

በክልሉ በገጠርና ከተማ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት የተሰሩ ስራዎች ውጤት አስገኝተዋል።



በሀረሪ ክልል ባለፉት አመታት የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች በገጠርና በከተማ የመጠጥ ውሃ ሽፋንን አሳድጓል።

በክልሉ የመጠጥ ውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ የአጭር፣  የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ ተይዞ ሲሰራ ቆይቷል። በእስካሁኑም በተሰሩ ስራዎች ከከተማው ባለፈ ለገጠሩ ህብረተሰብ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትና ሽፋን ማሳደግ ተችሏል።

የክልሉ መንግስት የህዝቡን የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሳደግ ከፍተኛ በጀት በመመደብና ከሚመለከታቸው አካልት ጋር በመቀናጀት ርብርብ ተደርጓል። በዚህም በነባር ፕሮጀክቶች ላይ ማስፋፊያዎችን በማድረግ የውሃ ምርት ማሳደግ ከመደረጉም በተጨማሪ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ተችሏል።

በክልሉ ኤረር ወረዳ የሚገነባው  የኤረር ኢባዳ የመስኖ ግድብ ፕሮጀክት አርሶ አደሩን የመስኖ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ለገጠሩና ለከተማው ህዝብ የመጠጥ ውሃ ፍላጎት በማሟላት ረገድ ሁነኛ ሚና የሚያበረክት ነው።በቀጣይም የክልሉ መንግስት በገጠርና ከተማ የህዝቡን ፍትሃዊ  ተጠቃሚነት ለማሳደግ  እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች አጠናክሮ ይቀጥላል።

የተሰጡ አስተያየቶች

Comments