የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በሐኪም፣ በአባዲር እና በአሚር ኑር ወረዳዎች ያስገነባቸውን የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች ህብረተሰቡ እንዲጠቀምባቸው ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
የሐረሪ ክልል ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከ92 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በከተማ በሚገኙ 6 ወረዳዎች አዲስ የተገነቡ እና ዕድሳት ያደረገላቸውን 72 የሚሆኑ የጋራ እና የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን በቅርቡ አጠናቆ ለህብረተሰቡ ያስረከበ መሆኑ ይታወሳል፡፡


